ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ የሞት አደጋወ እንደተከሰተ የከተማዋ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች የህዝብ ግኑኝነት አስታውቋል።
አባትና ልጅን ጨምሮ አራት የሚሆኑት ሟቾች ሂወታቸው ያለፈው በደቡባዊ የከተማዋ ክፍል የሚገኘውን ወንዝ ለምሻገር ሲሞክሩ ነው።
በወቅቱ ጥሎ በነበረው ከባድ ዝናብ ምክነያት ወንዙ ከመጠን በላይ ሞልቶ ነብር ነው የተባለው።
እስካሁንም የሁለቱን አስከሬን ብቻ ነው ማውጣት የተቻለው ቀሪዎቹን የአባትና ልጅ አስከሬንን ለማውጣት ፍለጋው ቀጥሏል።
ሌላኛው የሞት አደጋ የተከሰተው አንዲት ሴት ቦሌ ጃክፎስ አከባቢ የወንዝ ድልድይ በመሻገር ላይ ሳለች ተንሽራታ በመግባቷ በጎርፍ ተወስዳለች።