NEWS: በማላዊ የነጻነት ቀን አከባበር ላይ በተፈጠረ ትርምስ ስምንት ሰዎች ሞቱ-አብዛኞቹ ህጻናት ናቸው

 

ማላዊ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበትን አመታዊ ክብረ በኣል በዋና ከተማዋ ቢንጉ ብሄራዊ እስታድየም እያከበረች ባለችበት ወቅት በተፈጠረ መተፋፈግ ነው የሞት አደጋው የደርሰው።

ከሟቾች መካከል አብዛኞቹ ከአስር አመት በታች የሆኑ ህጻናት ምሆናቸው አደጋውን የከፋ አድርጎታል።

ከአከባቢው የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ፖሊስ በስታዲየሙ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀሙ የፈጠረው ትርምስ በተለይ ህጻናት ለሞት እንዲዳረጉ ሆኗል።

ከሞቱት በተጨማሪ 62 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የህክምና እርዳታ እየተሰጣቸውም ነው።

ማላዊ አንደፈረንጆቹ በ1964 ነው ከብሪታኒያ ነጻነቷን የተቀዳጀችው

ምንጭ-AP

Advertisement