ለንደን አሁንም የአውሮፓን የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት በመሳብ ቀዳሚዋ ሆናለች

                                        

ለንደን ከህብረቱ የመውጣት ውሳኔዋ በኋላም በአውሮፓ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ቀዳሚዋ ሆና ቀጥላለች።

በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በግል የቴክኖሎጂ ዘርፍ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ፓውንድ ኢንቨስትመንት መሳቧን የከተማዋ አስተዳደር የለንደን እና አጋሮቿ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በተመሳሳይ ወቅት በከተማዋ በማህበራት ደረጃ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ፓውንድ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ አድርገዋል፡፡

በአጠቃላይ በመንፈቅ ዓመት በከተማዋ የተመዘገበው የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ላለፉት 10 ዓመታት በተመሳሳይ ጊዜ ከተመዘገቡት እንደሚበልጥም ተነግሯል፡፡

የለንደን እና አጋሮቿ ኤጀንሲ ከተማዋ በመሰረታዊ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት አመቺነቷ እና ጥንካሬዋ አሁንም ቀዳሚ ሆና መቀጠሏን ነው የገለፀው፡፡

የብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት የመውጣት ጥያቄ የተወሰኑ አለመረጋጋቶችን ቢፈጥርም ለንደን ከሌሎች የአውሮፓ ከተሞች በተሻለ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት መሳቧን ነው የለንደን እና አጋሮቿ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ላውራ ኪለትሮን የተናገሩት፡፡

ለንደን ከደብሊን፣ ፓሪስ እና አምስተርዳም በላይ ኢንቨስትመንት መሳቧን ለጠንካሬዋ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

 

Advertisement