በደቡባዊ ጀርምን 18 ሰዎች በመኪና አድጋ ሂወታቸውን አጡ

46 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው የመንገድኞች አውቶብስ በሰሜናዊ ባቫሪያ አከባቢ ከአንድ ከባድ ትሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ ያስነሳው እሳት ለአደጋው መክፋት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለ።

30 የሚሆኑ ተሳፋሪዎችም በእሳት ከተያያዘው አውቶብስ ውስጥ መውጣት የቻሉ ቢሆንም የተወሰኑት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የጀርምኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርክል በደረስው አደጋው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጠዋል።

እሰካሁን አደጋው በምን ምክንያት እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም

አውቶብሱ  ጡርተኞችን አሳፍሮ ሳክሶኒ ከተባለችው አከባቢ እየተመለሰ ነበር

ከሟቾቹ መካከል አሽከርካሪው ይገኝበታል

ምንጭ-ቢቢሲ

 

Advertisement