ሻይና ቡና የጉበት በሽታን ለመከላከል – Coffe and Tea to Prevent Liver Damage

                                             

የጉበት በሽታ በብዛት ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤን ካለመከተል ጋር ተያይዞ የሚከሰት መሆኑ ነው በብዛት የሚነገረው።

በዓለማችን ውስጥ በገዳይነት ከተቀመጡት ውስጥም የጉበት በሽታ 12ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ታዲያ ከሰሞኑ የወጣ አዲስ ጥናት በቀን ውስጥ የተወሰነ ቡና ወይም ሻይ መጠጣት የጉበት በሽታ ተጋላጭነታችንን እንደሚቀንስ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪም ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ለጉበታችን ጤንነት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው ጥናቱ የሚጠቁመው።

በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ኢራስመስ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ጥናት እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ 2 ሺህ 424 ሰዎች ላይ ነው የተካሄደው።

ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ የጤና ምርመራዎችን እንዲያደርጉ የተደረገ ሲሆን፥ የ389 የምግብ እና የመጠጥ አይነቶች ውስጥ የትኞችን አብዝተው እና ደጋግመው ይጠቀማሉ የሚለውን መጠይቅ እንዲሞሉም ተደርጓል።

በጥናቱ ውስጥ የቡና አወሳሰድ በሶስት ተከፍሎ የታየ ሲሆን፥ ይህም ምንም የማይጠጡ፣ መጠነኛ በቀን ከ3 ሲኒ በታች የሚጠጡ እንዲሁም አብዝተው በቀን 3 እና ከዚያ በላይ የሚጠጡ በሚል ነው የተለየው።

ተመራማሪዎቹ በጥናታቸውም ቡናን አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች የጉበት በሽታ ተጋላጭነታቸው የቀነሰ ሆኖ ማግኘታቸውን የገለጹ ሲሆን፥ እነዚህ ሰዎች ለጉበት በሽታ እጋለጣለው በሚል የመሚፈጠርባቸው ስጋት ትርጉም አልባ ነው ይላሉ።

እንዲሁም ሻይ እና ቡናን አዘውትሮ መውሰድ በጉበት ላይ የሚከሰት በሽታን የመቀነስ እድሉ ከፍተኛ ሆኖ መገኘቱንም ነው ተመራማሪዎቹ የሚናገሩት።

ከዚህ በተጨማሪም ቡና እና ሻይን አዘውትሮ መጠጣት የጉበት ካንሰርን ከመከላከል ረገድም የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በኢራስመር ዩኒቨርሲቲ ሄፓቶሎጂስት የሆኑት ዶክተር ዳርዊሽ ሙራድ የሚናገሩት።

ምንጭ፦ www.upi.com/Health

Advertisement