የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች፡፡
1. ፍራፍሬ ፡- ፍራፍሬዎች ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖች ፣ ፋይበር እና አንቲ ኦክሲደንቶችን ስለሚይዙ በእለት ተእለት የምግብ ፕሮግራማችን ላይ ማካተት ጠቃሚ ነው፡፡
እንደ ፖም ፣ ሙዝ እና ሃብሃብ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ የምግብ አይነቶች ሲሆኑ እንደ ብርቱካን ያሉት ደግሞ እንዲወሰዱ አይመከርም
2. አትክልት ፡- የተለያዩ የአትክልት አይነቶችን መመገብ ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ ሲሆን በምግብ አዘገጃጀት ላይ የሚጨመሩ እንደ ነጭ ሽንኩርት እና የተለያዩ ማጣፈጫ ቅመሞች ግን እንዲወሰዱ አይመከርም፡፡
3. ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ፡- የጨጓራ ህመም ላለባቸው ሰዎች ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ተስማሚ የሆኑ ሲሆን ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ላይ ግን ህመሙን ሊያባብሱ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህም የሚስማማቸው ሰዎች ብቻ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡
4. ስጋ ዶሮ እና አሳ ፡ – እነዚህ ምግቦች የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ ሲሆን የማጣፈጫ ቅመሞች እና ቅባት ሳይኖርባቸው መመገብ ይቻላል ፡፡
5. ከሥጋና የመሳሰሉት ምግቦች ይልቅ በቀን ውስጥ የሚመገቡትን የምግብ ዓይነቶች ወደ ዳቦ፣ አጃ፣ ሩዝ፣ ድንች፣ ገብስ፣ ፓስታ፣ ማኮሮኒ ማዞር ለጤና ተመራጭ ነው፡፡
6. መጠጦች (Beverages) ፈሳሽ በሚገባ መውሰድ የጨጓራ ህመምን በከፍተኛ ሁኔታ ያስታግሳል፡፡ ንጹህ ውሀ መጠጣም ለሰውነታችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
እንደ ቡና ሻይ እና ለስላሳ መጠጦች የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲወስዷቸው አይመከርም፡፡
ምንጭ SciTechEthiopia/