ማስመለስን እንዴት መከላከል ይቻላል? – How To Prevent Vomiting?

                                                     

(በዳንኤል አማረ)
ማስመለስ ከማቅለሽለሽ በኋላ የሚመጣ ሲሆን በሆዳችን ውስጥ የሚገኙ የምግብ ይዘቶችን ሃይል በተቀላቀለበት መንገድ የማስወገጃ መንገድ ነው። በአንዳንድ አጋጣሚዎች ማስመለስ በፈቃድ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ብዙ ሰዎች የሚጠሉት ጉዳይ ነው።
✔ማስመለስን እንዴት መከላከል እንችላለን?
ማስመለስ ከመከሰቱ በፊት የምንከላከልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ ከነዚህም መካከል፦
1. የሚመገቡትን ምግብ ይመጥኑ
ብዙ ምግብ መመገብ በተለይ በግሪስ፣ ስኳርና ካሎሪ የተሞሉ ምግቦች ማስመለስ እንዲከሰት ያደርጋሉ። ይህን ለማስቀረት ትንሽ ምግብ በተደጋጋሚ ይመገቡ (በቀን 6 ጊዜ በጥቂቱ ይመገቡ)
2. ምግቡ ንጽህና በሚገባ የበሰለ መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ
ንጽህ ያልሆነ ምግብ ወይም ያልበሰለ ምግብ መመገብ የምግብ መመረዝ ያስከትላል። ይህም እንደ ማስመለስ ላሉ ብዙ ላልተፈለጉ ምልክቶች ይዳርገናል።
3. የአልኮል አወሳሰድዎን ይመጥኑ
ብዙ አልኮል በምንወስድበት ጊዜ ሰውነታችን ጎጂ የሆኑ መርዛማ ነገሮችን ለማጣራት ከባድ ሥራ ውስጥ ይገባል ይህም ጫና ማስመለስን ያስከትላል።
4. ከተመገቡ በኋላ በቀጥታ ስፖርት(እንቅስቃሴ) አያድርጉ
አካላዊ እንቅስቃሴ ለሰውነታችንም ሆነ ለአጠቃላይ ጤንነት በጣም አሰፈላጊ ነው። ነገር ግን ከተመገብን በኋላ ወዲያው ፈጣን እንቅስቃሴ ማድረግ ሆዳችን እንዲቆጣ ስለሚያደርገው ወደ ማስመለስ ሊያመራ ይችላል።
5.ለስላሳ መጠጦችን ይሞክሩ
6. ከመጥፎ ሽታ ይራቁ
መጥፎ ሽታ ወይም ጠረን ያለበት አካባቢ በሚገኙበት ጊዜ በሆድዎ ውስጥ ያለው ምግብ ለመውጣት የማይፈታተነው ሰው የለም ስለዚህ የማስመለስ ዕድልዎን ለመቀነስ ከመጥፎ ሽታ አካባቢ በፍጥነት ራስዎን ያርቁ።
7. ቀዝቃዛ አካባቢ ይምረጡ
እርጥብ ቀዝቃዛ ንጽህ ጨርቅ በፊታችን ወይም በግንባራችን ላይ መያዝ ወይም በኤሌክትሪክ ፋን ፊትለፊት ላይ መቀመጥ ቀዝቃዛ አየር በመፍጠር የሆድ መቆጣትን ይቀንሳል።
8. ትንሽ እንቅልፍ ይተኙ
ጥሩ ስሜት የማይሰማዎት ከሆነ እረፍት እንዲያደርጉ ሁሌም ይመከራል። ከሆድ ምቾት አለመሰማት በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የድካምና የመልፈስፈስ ስሜት ተሰምቶዎታል ማለት ከሌሎች ቀኖች በተለየ ሁኔታ እረፍት ያስፈልግዎታል ማለት ነው። ስለዚህ እንቅልፍ መተኛት ማስመለስን ለመከላከል ይረዳዎታል።
9. የመዳሰስ ስሜትዎን ያነቃቁ
የአንድን ሰው የመዳሰስ ስሜት ማነሳሳት የሚያስፈልግበት ዋናው ምክንያት ማስመለስን ለመከላከል ነው። ክንድን መቆንጠጥ፣ የታችኛውን ከንፈር መንከስና ፀጉርን መንጨት(መጎተት)። የሚሰማወት ጥቂት ህመም ሃሳብዎን ከማስመለሱ ላይ እንዲቀይሩ ይረዳዎታል።
10. ሃሳብዎን ይበታትኑ
ስለ ማስመለስ ወይም ማቅለሽለሽ ብቻ ከሚያስቡ ይልቅ በጣም ጣፋጭ የሆነ ወሬ ማውራት ወይም በጣም የሚወድትን የቴሌቪዢን ፕሮግራም መከታተል አእምሮዎን ከዚህ ለማሸሽ ይጠቅማል።
ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement