የ101 ዓመቷ አዛውንት በ100 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል – The 101-year-old Man Who Compete in 100-meter Race has Become a Gold Medalist.

                                 

የ101 ዓመት ህንዳዊ አዛውንት በ100 ሜትር ሩጫ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን መቻላቸው ተነግሯል።

ማን ኩር የተባሉት የ101 ዓመት ህንዳዊት አዛውንት በኒውዚላንድ ኦክላንድ የተዘጋጀውን የ100 ሜትር ሩጫ በ1 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ ማጠናቀቅ ችለዋል።

አዛውንቷ የ100 ሜትር ሩጫውን ያጠናቀቁበት ሰዓትም በአሁኑ ጊዜ በ100 ሜትር የዓለም ክብረወሰን የያዘው ዩዜይን ቦልት ከገባበት በ64 ነጥብ 42 ሰከንድ የዘገየ መሆኑ ተነግሯል።

ኩር ከውድድሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት፥ “በውድድሩ ተዝናንቻለው፤ አንደኛ በመውጣቴም ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። 

“አሁንም ቢሆን በሌሎች ውድድሮች ላይ በድጋሚ እወዳደራለው፤ እጅ መስጠት ብሎ ነገር የለም፤ በዚህ ቀን አቆማለው ብዬ የወሰንኩት ቀን የለም” ሲሉም ተናግረዋል።

ኩር በአትሌቲክስ ውድድር ላይ መሳተፍ የጀመሩት ከስምንት ዓመት በፊት ሲሆን፥ ውድድር ላይ መካፈል ሲጀምሩም የ93 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ነበሩ።

ከዚያን ጊዜ በፊት ገን ምንም አይነት ስፖርታዊ ውድድር ላይ የመካፈል ልምድ ያልነበራቸው ሲሆን፥ በልጃቸው ጋርዲቭ ሳይኒህ አማካኝነት ነው ኩር ወደ ውድድር ዓለም የገቡት።

በጊዜውም አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ውድድር ላይ መካፈል እንደሚችሉ የተናገራቸው ሲሆን፥ ከዚያ በኋላም እናት እና ለጅ በዓለም ዙሪያ በርካታ ዓለም አቀፍ የአዛውንቶች ውድድር ላይ ተካፍለዋል።

እስካሁን ከተወዳደሩባቸው የውድድር መድረኮችም 17 የወርቅ ሜዳሊያ መሰብሰብ መቻላቸው ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ www.uk.news.yahoo.com

 

Advertisement