ሰዎች ሳያስቡት በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እንደሚላበሱ አንድ ጥናት አመለከተ – Research Showed That Unknowingly People Could Adopt People’s Behavior Nearby.

                                              

የፈረንሳይ ዓለም አቀፋዊ የጤና እና የህክምና ምርምር ኢንስቶትዩት ተመራማሪዎች የሰዎች የባህሪ ወይም የአዕምሯዊ ተግባራት ለውጥ እንዴት እንደሚከሰት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በጥናቱ መሰረት ሰዎች በማህበራዊ ተራክቦ ሳቢያ የአመለካከት መደበላለቅ እና የባህሪ ለውጥ ያጋጥማቸዋል፡፡

ይህም ማለት ሰዎች በአቅራቢያቸው ካሉ ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን የመላበስ ወይም የመቅዳት ዝንባሌ በአዕምሯቸው ላይ ያርፋል ማለት ነው፡፡

የሰው ልጅ ሰነፍ ወይም ብርቱ ለመሆኑ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችለው በቅድሚያ በአቅራቢያው ያለን ሌላ ሰው ነው፡፡

እንደ ጠንቃቃነት፣ ስንፍና እና ትዕግስት ማጣት ያሉ ባህሪያትን ሰዎች ሳያስቡት በአቅራቢቸው ካሉ ሰዎች የመውረስ አጋጣሚዎች መኖራቸውን ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

እነዚህ ባህርያት እንዴት ወደ ሰዎች እንደሚጋቡ ለማጥናት የሞከሩት ተመራማሪዎችም ምክንያቱ የሰዎች ባህሪ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ የሚሳርፍ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የሰዎች የአመለካከት ወይም የአዕምሯዊ ተግባራት ለውጥ በአቅራቢያቸው ባሉ ሌሎች ሰዎች ተፅእኖ እንደሚከሰት በሂሳባዊ እና ስነልቦናዊ የጥናት ስልት ግንኝታቸውን ገለፀዋል፡፡

በጥናቱ 56 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን እነኝህ ሰዎች የሚሰጡት ውሳኔ ፍጥነት እና መዘግየት፣ ለሁኔታዎች ያላቸው ስሜት በሙሉ ተጠንቷል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየውም ሰዎቹ ለድንገቴ ወይም የአጋጣሚ የሃሳብ መሰረቅ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ሰዎቹ ውሳኔዎችን ወይም ድርጊቶችን የሚያደርጉት በአቅራቢቸው ሰዎች ሲደርጉት በማየት ሀሳባቸው በመሰረቁ የሌሎችን ተግባር ወይም አመለካከት የመላበስ አጋጣሚ ስለሚፈጠር ነው ተብሏል፡፡
ጥናቱ የሰዎችን እና የእንስሳትን ተነጻጻሪ የማሰብ ተመሳስሎ ለማወቅ እንደሚረዳም ተነግሯል፡፡
ምንጭ፡-www.dailymail.co.uk

Advertisement