ጥቅል ጎመንን – Cabbage

                                                        

ብዙውን ጊዜ በተለምዶ ተወስዶ የምግብን አይነት ለማብዛት እንጠቀምበታለን፡፡ በMedical News Today ላይ በወጣው ጥናት መሰረት ጥቅል ጎመንን ከገበታችን አለመለየት የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል፡፡ ጥልቅ ጎመንን በስፋት በሚጠቀሙ ሀገራት/አካባቢዎች/ ያሉ ሰዎች የአንጀት ካንሰርን መከላከል እንደሚችሉ ጥናቶቹ ጠቁመዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ጥቅል ጎመን የፋይበር ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡
በውስጡ ያሉ ከፍተኛ ኬሚካሎች ተፈጥሯዊ ናቸው፤ በሰውነታችን ውስጥ የምግብ መፈጨት ስርዓትን ቀልጣፋ እንዲሆን ከማገዙም በላይ ከካንሰር አይነቶች መካከል የጡትና የማህፀን ካንሰርን እንደሚከላከልም ይጠበቃል፡፡
ከቫይታሚን C እና ከቫይታሚን A የሚገኘው ቤታካሮቲን በውስጡ ያለ በመሆኑም ለረጅም ጊዜ ወጣት ሆኖ ለመቆየት /በቶሎ ላለማርጀት/ ትልቅ ሚና አለው፡፡
ቤታካሮቲን በካሮት ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ለአይን ጤንነት ይመከራል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ይኸው ንጥረ ነገር በጥቅል ጎመን ውስጥ ስለሚገኝ ለአይን ጥራትና ጤንነት ይበጃል፡፡ ነፍሰጡር ሴቶችም አዘውትረው ቢሚገቡት ለፅንሱ ደህንነት ጠቃሚ ነው፡፡
በሰውነታችን ውስጥ አላስፈላጊ የሆነ ኮሌስትሮል እንዳይከማች ከማድረጉም ጎን ለጎን የልብ ህመም ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ዓለማችን ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ከመጡ ነገሮች መካከል አንዱ አልዛይመር (ከፍተኛ የሆነ የመርሳት ችግር) ነው፡፡ ይህን ለመከላከል ደግሞ ጥቅል ጎመን ጠቃሚነቱ ተረጋግጧል፡፡
ክብደትን ለመቀነስ ከማገዙም ባሻገር ቆዳን እንደሚያጠራ ይታመናል፡፡ በተለይም ብጉር ያለባቸው /የሚበዛባቸው ሰዎች ቢያዘወትሩት መልካም ነው ተብሏል፡፡
ኢንፌክሽንን እንደሚከላከል፤ በጥቅሉ በሽታን የመከላከል አቅምን እንደሚጨምር ጥናቱ አመላክቷል፡፡

ምንጭ፦ Medical News Today

Advertisement