የኮምፒውተርዎን ደህንነት ለመጠበቅ

               

ኮምፒውተርዎን ረዘም ያለ ጊዜ ያለ መቆራረጥ እና ችግር እንዲገለገሉበት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከአቀማመጥ ጀምሮ በየዕለቱ የሚሰራበትን ጊዜ እስከመወሰን የደረሰ ክትትል በማድረግ ኮምፒውተሩን በአግባቡ መገልገል ይችላሉ።

በአግባቡ መገልገል ከቻሉ ለጥገና የሚያወጡትን ወጭም ቀነሱ ማለት ነው።

ኮምፒውተርዎን ረዘም ያለ ጊዜ ያለ ችግር ለመጠቀም ደግሞ እንዲህ ያድርጉ፤

እንዳይሞቅ ማድረግ፦ በርካታ ስራ ከመስራቱ ጋር ተያይዞ ኮምፒውተርዎ በከፍተኛ ሁኔታ ይሞቃል።

ቀዝቀዝ ያለ የማስቀመጫ ቦታ በመምረጥ ኮምፒውተሩን እንዳይሞቅ ማድረግ ያስፈልጋል።

ኮምፒውተሩን የታፈነ ቦታ አለማስቀመጥና አየር እንደ ልብ በሚዘዋወርበት ስፍራ መገልገል።

ከአቧራ ብናኝ መከላከል፦ ከአቧራና ከነፍሳት መከላከልና ማጽዳት፤ በጣም የበዛ ሙቀትም ሆነ ቅዝቃዜ ለኮምፒውተሩ ደህንነት አደገኛ ነው።

አቧራ በብዛት ከገባበት የኮምፒውተሩን ማቀዝቀዣ እንደ ልብ እንዳይዞርና እንዳይሰራ በማድረግ ለከፍተኛ ሙቀት ይዳርገዋል።

ከፍተኛ ሙቀት ደግሞ ለኮምፒውተሩ እድሜ ማጠር ምክንያት ነውና ከአቧራ ብናኝ ይጠብቁት።

ከዚህ ባለፈም በወር አንድ ጊዜ ለኮምፒተርዎ አጠቃላይ ፍተሻ ማድረግና አላስፈላጊና የሚያጨናንቁ ፋይሎችን ማጥፋት።

ኮምፒውተሩን በማጠፋፋትና ሶኬቶችን በመነቃቀል ውስጡን ከፋፍቶ ማጽዳትና በደንብ አናፍሶ መግጠምና መጠቀም።

ስራዎን ሲጨርሱ ማጥፋት፦ ምንጊዜም የዕለቱን ስራ ሰርተው ሲጨርሱ ኮምፒውተሩን ማጥፋትዎን አይርሱ።

ይህን ሲያደርጉ ኮምፒውተሩ እንዳይሞቅና ለቀጣዩ ቀን በደንብ ሃይል እንዲሰበስብ ያደርገዋል።

ከዚህ ባለፈም መረጃዎን በበርባሪዎች እጅ ከመግባት ይታደጉታል።

ባትሪ፥ የኮምፒውተሩ ባትሪ እንዳይጎዳ ቋሚና መብራት ቢጠፋ እንዳይቋረጥ የሚያደርግ ዩ ፒ ኤስ መጠቀም።

አንዳንድ ጊዜም የላፕቶፑን ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆና ሞልቶ መገልገል መልካም መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

አግባብ የሆኑ እና የኮምፒውተሩን ፍጥነት እንዳይቀንስ የሚረዱ አንቲ ቫይረሶችን መጫን። 

ኮምፒውተሩን በበዙ ፋይሎች አለማጨናነቅና በውስጡ የሚይዛቸውን መረጃዎች መጠን ማሳነስም መልካም ነው።

ምንጭ፦ FBC (ኤፍ ቢ ሲ)

Advertisement