በየእለቱ በምንጠቀማቸው ቁሶች ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል የከፋ የጤና ጉዳት ያስከትላል

                                                       

በየእለቱ በምንጠቀማቸው ቁሶች ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል የከፋ የጤና ጉዳት እንደሚያደርስብን ከሰሞኑ የወጣ ጥናት አመልክቷል።

የፕላስቲክ የውሃ መያዣ፣ ከብረት የተሰሩ የምግብ ማሸጊያዎች፣ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎች፣ እንዲሁም የመዋቢያ ቅባቶች /ኮስሞቲክስ/ ውስጥ ያለ ኬሚካል ነው ለከፋ ጉዳት የሚያደርሰው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

ተመራማሪዎቹ በእነዚህ ቁሶች ውስጥ የሚገኘው ኬሚካለ ሆርሞኖችን የሚረብሽ ሀዛርደስ ነው ያሉ ሲሆን፥ ይህም ለበርካቶች የጤና ጠንቅ ሲሆን ይስተዋላል ብለዋል።

የኒው ዮርክ የጤና መእከል ባወጣው ሪፖርት መሰረት፥ ለዚህ ኬሚካል በአነስተኛ መጠን ተጋላጭ መሆን ከ15 አይነት የጤና ችግር ጋር ግንኙነት አለው፤ ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑት እስከሞት ሊያደርሱ የሚችሉ ናቸው ይላል።

በጥናቱ መሰረት ኬሚካሉ እንደ የፕላስቲክ የውሃ ማሸ ጊያዎች እና መሰል ቁሶች በኩል ወደ ውስጣችን ከገባ በኋላ ቀስ በቀስ ራሱን በመገንባት የከፋ ጉዳት ያደርሳል።
ጥናቱ በአሜሪካ የተሰራ ሲሆን፥ ጥናቱን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት እንደፈጀባቸው ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ።

የጥናት ቡድኑ ከ5 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ሆነው ከተሳተፉት ላይ የደም እና የሽንት ናሙና በመውሰድ ጥናቱን እንዳካሄደም አስታውቋል።

በዚህም በእለት ተእለት ኑሮዋቸው ውስጥ ለኬሚካሉ የተጋለጡ ሰዎች፥ ለተለያዩ የአእምሮና የባህሪ መዛባቶች፣ የወንድ የመካንነት ችግር፣ ከመጠን ላለፈ ውፍረት፣ የስኳር በሽታ እንዲሁም ለተወሰኑ የካንሰር አይነቶች የተጋለጡ መሆኑን ለይተናል ነው የሚሉት። 

የጥናት ቡድኑ መሪ የሆኑት ዶክተር ሊዮናርዶ ትራሳንድ፥ በጥናቱ የተገኘው ውጤት የኢኮኖሚ በመለወጥ ምክንያት እየደረሰ ላለው ጉዳት እና የህክምና ወጪ ለምን እየጨመረ መጣ ለሚለው ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው ብለዋል። 

ዶክተር ሊዮናርዶ አያይዘውም መንግስታት ለሀገራቸው ዜጎች ሲባል በገበያ ላይ የሚውሉ ቁሶች የኬሚካል ተጋላጭነታቸው ቢቆጣጣሩ መልካም ነው ብለዋል።

ምንጭ:- FBC(ኤፍ.ቢ.ሲ) 

Advertisement