ዊንዶውስን የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች በቫይረስ መጠቃታቸውን ለመለየት…

                                                      

በዓለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ዘንድ በብዛት ጥቅም ላይ ከሚውሉት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ውስጥ ዊንዶውስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በብዛት ጥቅም ላይ እንደመዋሉ ሁሉ እንደ ለኮምፒውተር ቫይረስ፣ ቶርጃን እና ማልዌሮች የመጠቃት እድሉም ያንኑ ያክል ከፍተኛ መሆኑ ነው የሚነገረው።

 ዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን የሚጠቀሙ ላፕቶፕም ይሁን ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ያለን ከሆነ ኮምፒውተራችን በቫይረስ መጠቃት አለመጠቃቱን ለመለየት አዳጋች ሊሆንብን ይችላል። 

ኮምፒውተሮች በቫይረስ ሲጠቁ በብዛት ከሚስተዋልባቸው ምልክቶች ውስጥ ኮምፒውተራችን እኛ ሳንፈልግ በራሱ ጊዜ እንደ አዲስ ዘግቶ መነሳት ወይም “ሪቡትስ” ማድረግ፣ አልታዘዝ ብሎ እዛው ደርቆ ለተወሰነ ጊዜ መቅረት እና አሁንም አሁንም ስራ የማቆም /ክራሽ/ ማድረግ ይገኙበታል።

ከዚህ በተጨማሪም በምስሉ ላይ የተገለጹት 10 ምልክቶች ኮምፒውተራችን በቫይረስ መጠቃቱን የሚያረጋግጡልን ናቸው ተብሏል።

 ኮምፒውተራችንን ከቫይረስ ለመከላከል…

ኮምፒውተራችን በቫይረስ እንዳይጠቃ ለመከላከል ተዓማኒነት ከሌላቸው ድረ ገጾች ላይ መረጃዎችን አለማውረድ ወይም ዳወንሎድ አለማድረግ።

አስተማማኝ የሆኑ አንቲ ቨይረሶችን በኮምፒውተራችን ላይ መጫን እና በየጊዜው የሚያስፈልገውን ማሻሻያ ወይም አፕዴት ማድረግ።

ለላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮ ዊንዶውስ 10 ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ከሆነ ደግሞ ዊንዶውስ ዲፌንደርን በየጊዜው አፕዴት እያደረግን መጠቀም ይመከራል።

ምንጭ :- FBC(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Advertisement