“የተመኘሀትን ሴት ማንም ትሁን የራስህ ልታረጋት ትችላለህ” (ምርጥ የሆነ ሳይኮሎጂ)

ከታደለች ስዩም

ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሚሊዮን ብር ወይም ብዙ ታላቅና ውብ
ነገር ያላቸው ያህል እንዲሰማቸው አድርጎ ለሚመለከታቸው
በውስጣቸው ቦታ የመስጠት ዝንባሌያቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር
ግን በየሁኔታዎቹ አጋጣሚ ለጥቂት ሰከንድም ቢሆን የእሷን
ደስታ ሊጨምርላት የሚችሉ የተለያዩ ሌሎችም በርካታ ነገሮችን
ልታውቅላት የሚያስፈልግና ለአንተም ጥሩ ግንኙነት ለመፍጠር
ወሳኝ ጉዳይ ይሆናል፡፡
ሌላው ደግሞ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ንግስት አድርገው
የማሰብ ዝንባሌው ያላቸው ስለሆነ ከእሷ ሳይመጣ ይህን ራሷን
የመካብ ስራ ከአንተ ይውጣና በውስጧ ይህ ስሜት እንዲሰማት
አድርጋት፡፡ እነዚህን ነገሮች እንደመቀስቀሻና ራሷን ማንቂያ
አድርጋ እንድታስብ አድርገህ ከያዝካት ምንጊዜም ካንተ
ለመለየት ሙከራው ቀርቶ ይህን ነገር ማሰብ እንደ መጥፎ
ህልም ያባንናታል፡፡
ለአንተ ንግስትህ እንደሆነች በድርጊትም ሆነ በንግግርህ
ከገለጽክላት ሁሌም ጥሩ ስሜት ስለሚሰማት እንደማግኔት
ልብህ ላይ ትጣበቃለች፡፡ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ስሜታቸውን
ተከትለው ይፈሳሉ፡፡ በጥልቁ ስሜታቸው ከመጣህባቸው
አይመለሱም፡፡ ለዚህም ስሜቷ ሲነካ የሚገርሙ ምላሾች
አሏት፡፡ ይህንን ሁሉ ስሜታቸውን የማይረዱላቸው ወንዶች
ወይም መጀመሪያውኑ ሴቷን እየፈለጋት ከንግግሩ ጀምሮ እስከ
አቀራረቡ ድረስ ገገማ ዓይነት የሚሆንባቸው ወንድ
ያናድዳቸዋል፡፡ ሴትን ልጅ ቀርቦ ማናገርና ጥሩ ግንኙነት
መፍጠር የብዙ ወንዶች ችግር ነው፡፡ ከተዋወቁና ጥሩ የሆነ
መቀራረብ ውስጥም እያሉ ወንዶች አሁንም ትልቅ የሆነ
የግንኙነት እንቅፋት ይፈጠርባቸዋል ወይም በራሳቸው ጊዜ
ይህንን ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡ ታዲያ በጣም ወሳኝ የሆኑና
የትኛውም ወንድ ሊያውቃቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡
እነዚህ የመልካም ግንኙነት ቅመሞች ወንድ ልጅ ከመጀመሪያ
ጀምሮ ውስጡ የደነገጠላትና ለፍቅር የሚመኛትን ሴት ቀርቦ
ከማናገር ጀምሮ እንዴት በጥሩ ግንኙነት ወደ አስደሳች የፍቅር
ሽሚያ ውስጥ መግባት አለበት የሚለውን ያጠቃለለ ነው፡፡
ታዲያ በፍቅር ሽሚያ ውስጥም ሆነው ወንዶች ቀጣይ የሆነ
አስደሳች ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ
ይገባል፡፡
አስቀድሜ የመጀመሪያ የፍቅር ግንኙነት ችግር የሚለውን ሀሳብ
ላብራራ፡፡ ይህም ጎልማሳ የሆኑ ወንዶች ከአንዲት ሴት ጋር
ለሶስት ወይም ለአራት ወር አብረው ይቆያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእሷ
ጋር በስልክ በሳምንት ሁለቴ ብቻ ሲገናኙ በአካል ደግሞ አንድ
ጊዜ ብቻ ይገናኛሉ እንበል፡፡ ታዲያ በዚህ የረጅም ጊዜ ግንኙነት
ጥሩ የሆነ መግባባትን ለመፍጠር አልቻሉም፡፡ ይህ አይነት
ችግር ያለባቸው ብዙ ወንዶች ከመሆናቸው አንፃር የሚከተሉትን
አጠቃላይ መደምደሚያ ማንሳት ይቻላል፡፡ እነዚህ የሚነሱ
ሀሳቦች መሰረታዊና በወንዶች ላይ በብዛት የሚታዩ ችግሮች
ናቸው፡፡ ችግሩን አውቀውት ወደ ተሻለ የፍቅር መፍትሄ
የሚመልሳቸውም ጭምር ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
1.
ከተቃራኒ ጾታ ጋር ቀርቦ ለመነጋገር በራስ የመተማመን ችሎታ
ማነስ፡-
ብዙ ጊዜ እነኚህ ሰዎች በአንድ ቤተሰብ ብቻ (single
parent) ያደጉ ወይም እህት ኖሯቸው የማያውቁ ናቸው፡፡
በዚህም ስለሴቶች ያላቸው እውቀትና ለሴት ልጅ ያላቸው
አመለካከት የተዛባና ፍራቻ የነገሰበት ይሆናል፡፡ ከሴቶች ጋር
አብሮ ማደግ በቅርብ የሴቶች ባህሪ ምን እንደሚመስል
ለማወቅ ስለሚያስችል በዚያም ወንድ ልጅም ሲያድግ ስለ
ሴቶች ባህሪ ጥሩ እውቀት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ስለሴቶች
ባህሪ ማወቅ ደግሞ ሴትን ልጅ በምን መልኩ ለፍቅር ማቅረብ
እንዳለብህ ያሳውቅህ፡፡

2. የትላልቅ ቦታዎች ፍራቻ፡-
ትልቅ ቦታ ለመግባት ማለትም ከሀብታም ሰዎች የመዝናኛ ቦታ
ወይም ትላልቅ ሆቴሎች ገብቶ ለመዝናናት አንዱና ትልቁ
ችግራቸው ነው፡፡ እነኚህ ወንዶች እንዴት ለብሰው መሄድና
እንዴት መመገብ እንዳለባቸው አናውቅም ብለው በውስጣቸው
ስለሚያስቡና ራሳቸውን ስለሚያሳንሱ በእንደዚህ አይነቱ ቦታ
አይገኙም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ከሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት
የተወሰነ ስለሚሆን ብዙ እውቀት (Information) ስለሌላቸው
ብዙ አዝናኝ የሆነ ነገር ለሴቶች ለማቅረብ ያዳግታቸዋል፡፡
ሴቶች ደግሞ ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ቦታና ሁኔታን ስለሚጠሉ
ከለመዱት ወጣ ባለ መልኩ ራሳቸውን የሚያሳድጉበትን ታላላቅ
ነገሮችና መዝናኛዎችን ይመርጣሉ፡፡

3. ሴቶችን በምን ዘዴ መቅረብ እንደሚቻል አለማወቅ፡-
ብዙ ጊዜ ሴቶችን ለማጥመድ በሆነ ርዕስ ላይ አብረሃት
እውቀትህን ለማሳየት ከመጽሐፍት ያነበብከውን ታካፍላታለህ፡፡
ነገር ግን ከአንዲት ሴት ጋር የሆነ ትውስታን ሊጭር የሚችል
ግንኙነት ካልፈጠርክ ከሰከንድ በኋላ ትረሳሃለች፡፡ ታዲያ ሴትን
ልጅ በተለያዩ ዘዴዎች ልትቀርባትና ከቀረብካትም በኋላ ነገሯን
አንበብህላት ታላቁን የጨዋታ ሚናህን ልትወጣ ይገባሃል፡፡
ታዲያ በምትፈጥረው ድንቅ አጋጣሚዎች ሁሉ አንተነትህን ወደ
ፍቅር ሰው የምትለውጥ አድርገህ አቅርበው፡፡ ጨዋታህ የፍቅር
ምልክት ቢኖረውም ጠርሷ ላይና ጆሮዋ ላይ ብቻ የሚቀር
ሳይሆን ጨዋታህ ሁሉ ፍቅርህን ልቧ ላይ የሚተክል መሆን
እንዳለበት ራስህን አዘጋጅተህ ቀጥል፡፡ ለፍቅርህ እንቅፋት
ከሚሆኑ ሰዎችም ራሳችሁን አርቁ፡፡ የማይመቹ ነገሮችን
ትታችሁ ወደሚመቻችሁ ነገር ራሳችሁን አምጡት፡፡
4. በመጀመሪያ ሴቶች ስትቀርብ ተለሳልሰህና በጥሩ ባህሪ
ይሁን፡-
የሚያስደስት ባህሪ ያለህ መስለህ መቅረብ ወይም በጣም ጥሩ
የሚባል ወንድ ሆነህ ራስህን ማቅረብ ትልቅ ሚና
ይጫወትልሀል፡፡ ይህንን ለቅርበት ብለህ በራስህ ላይ
ያመጣኸውን ባህሪህን ትተህ ወደ እውነተኛ ባህሪህ እንዴት
መመለስ እንደምትችል ወይም ጥሩ ባህርይ ተፈጥሯዊና
ቀጣይነት ያለው ግን ፍቅርን የሚናገር መሆኑን ካላወቅህ
ከሴቶች ጋር ሁሉ ጥሩ ሰው የሚባል ሰው ሆነህ ብቻ ከቀረብክ
ያቺ ሴት እቤቷ ሄዳ ስለ አንተ ጥሩነት ብቻ ታወራለች፡፡ ነገር ግን
እንደ አንድ ጥሩ ወንድምና ጓደኛዋ ብቻ ስለምትቆጥርህ ከሌላ
ወንድጋር ሌላ የፍቅር ግንኙነት ትመሰርታለች፡፡ ስለዚህ ጥሩ
ሰው ብቻ ሳትሆን ጥሩ የፈቅር ሰው ወይም የፍቅር አጋር
መሆንም እንደምትችል ማሳየት አለብህ፡፡
5. ሁል ጊዜ የሚያስደስታትን ነገር እወቅላት፡-ከምንም በላይ
ሴቶች የውስጣቸውን ምቾት የሚጠብቅላቸውን ወንድ
ያመቻቸዋል፡፡ ታዲያ ምን እንደሚያስደስታት ማወቅ የአንተ
የወንዱ የቤት ስራ ይሆናል ማለት ነው፡፡ አስደስታት ምቾቷንም
በሚገባ ጠብቅላት፡፡ ይህን እያደረክ ስትመጣ የበለጠ
ግንኙነትህን አስደሳች ታደርገዋለህ፡፡ ምክንያቱም ስሜቷን
ስትጠብቅላት ሁሌ አንተን ብቻ ትላለች፡፡ ያን ጊዜ ፈላጊና
ተፈላጊ ተገጣጠሙ ማለት ነው፡፡

6. የፍቅር ሰው መሆንህን አሳውቃት፡-
በማንኛውም የግንኙነት አጋጣሚ ወንድሟን ወይም እህቷን
ወይም እናቷን መስለህ ሳይሆን ፍቅረኛዋ እንደሆንክ መስለህ
ወይም ሆነህ ቅረባት፡፡ ይህም ማለት እንክብካቤና የእናትነት
አይነት ስሜት ከመጠን በላይ አታብዛባት፡፡ እንክብካቤህ
በጥቂቱና በጥበብ ሆኖ ጨዋታዎችህ ግን ፍቅር ፍቅር
የሚያሸትቱህ ሊሆን ይገባል፡፡ የብዙ ወንዶች ችግር ውስጣቸው
ለፍቅር ከሚፈልጋት ሴት ጋር በጓደኝነት ቀርበው በኋላ ላይ ወደ
ማንነታቸው መለወጥ ነው፡፡ ነገር ግን በየትኛውም አይነት
አቀራረብ ቅረባት፡፡ ብዙ ጊዜ ሳትወስድ ግን አቀራረብህን ወደ
ፍቅር ለውጠው፡፡ ጥሩ የፍቅር ሁኔታን ከሰጠኻትና ያንተ መሆን
ከፈለገች እሷም ብዙ
ብዙ ጊዜ ሳትወስድ ግን አቀራረብህን ወደ
ፍቅር ለውጠው፡፡ ጥሩ የፍቅር ሁኔታን ከሰጠኻትና ያንተ መሆን
ከፈለገች እሷም ብዙ ጊዜ አታባክንብህም፡፡ ያኔ ቅርርባችሁን
ወደ ጣፋጭ የፍቅር ግንኙነት በቀላሉ መቀየር ትችላለህ፡፡

7. አማላይነትህን ተጠቀምበት
የራስህን ማንነት ከመጠበቅ ጀምሮ ጥሩ የሚባል ስብዕና ያለው
ወንድ ሆነህ ቅረባት፡፡ ባገኘኸው አጋጣሚ አማላይ ሆነህ
ቅረባት፡፡ በአንተ መልካምና አማላይ የሆነ አቀራረብ ውስጥ
ለእሷም ጥሩ ነገር የምትፈጥርና የበለጠ አምራና ጎልታ
እንድትወጣ ታደርጋታለህ፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ሁኔታዎች
ውስጥ ከአንተ ጋር ተነፃፃሪ በሆነ መልኩ ራሷን አማላይና
ማራኪ በሆነ መልኩ ለማቅረብ ስለምትጨናነቅ ነው፡፡ እነዚህንና
መሰል ነገሮችን በሚኖራችሁ ቅርርብ ውስጥ የምትተገብራቸው
ከሆነ ግንኙነታችሁ ጣፋጭና ድንቅ የፍቅር ጊዜ ይሆንላቸዋል፡፡
ሰዓቶችና ቀናት ሁሉ ያጥራቸዋል፡፡ ያኔ የፍቅር መቀሶችህን
ለይተህ በማወቅህ በፍቅር ቅመሞች የመለወጥና
የግንኙነታችሁም ታላቅ የፍቅር ንጉስ የመሆን ዕድሉ ይኖርሀል፡፡
አማላዬ የሚለውን ዜማም ጀባ በላት፡፡ እሷም አንተ የእኔ… የእኔ
የነብሴ ክፋይ ትልሀለች፡፡

ምንጭ: //www.mahderetena.com

Advertisement